Gebeya Search

Jafer Books 📚

32,000 subs • 162 products
የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን !!
አድራሻችን
ለገሃር ተወልደ ህንጻ
አራት ኪሎ ብርሃና ሰላም ፊት ለፊት
አብርሆት ቤተመጻሕፍት ግቢ ውስጥ
ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት
ሳሪስ አዲሱ ሰፈር
ጀሞ

ለቴሌግራም https://t.me/Jafbok

ለፌስቡክ https://www.facebook.com/jaferbookshop?mibextid=ZbWKwL

ለዌብሳይት www.jaferbooks.com
Page 4 of 17
(Showing 31 - 40 of 162 products )

17 days ago

ETB A

ራሳችሁን ከውቅያኖስ ዳርቻ እንደቆማችሁ አስቡ። ውቅያኖሱ እናንተ በሕይወታችሁ ቆይታ ወቅት የሚያጋጥማችሁን የተትረፈረፈ ሀብት ይወክላል። ውቅያኖሱ ውስጥ ያለውን ሐብት ለመውሰድ ምን ዓይነት የፈሳሽ መያዣ ይዛችኃል? ማንኪያ፣ ቀዳዳ ያለው ባሊ፣ የወረቀት ኩባያ፣ ትንሽ የባኞ ገንዳ፣ በርሜል ወይስ ወንፊት? የፈሳሽ መያዣው አዕምሯችሁን ይመክራል። ትልቅ ባሰባችሁ ቁጥር ትልቅ ነገር የማግኘት ዕድል ይጨምራል። በርግጥ በተትረፈረፈው ውቅያኖስና በፈሳሽ መያዣው መካከል የቧንቧ መስመር በመዘርጋት ያልተቋረጠ አቅርቦት እንዲኖር ማድረግ ትችላላችሁ። በርካታ ሰዎች የየራሳቸው የፈሳሽ መያዣ ይዘው ውቅያኖሱ ዳርቻ ቆመው ሊሆን ይችላል። አስገራሚው ነገር ሰዎች እንደፈለጉ እየተመላለሱ ከውቅያኖስ ውሃ ቢወስዱም ውቅያኖሱ ተቀድተው የማያልቅና ለሁሉም ተትረፍርፎ የሚበቃ ውሃ ነው። ተዘውታሪው በሆነ መልኩና በየዕለቱ ስለዚህ የተትረፈረፈ ውቅያኖስ አስቡ ወደ ውቅያኖሱ በተመለሳችሁ ቁጥር የፈሳሽ መያዣችሁ ጥልቀትና ስፋት (አእምሯችሁን) እንደፈለጋችሁ መጨመር እንደምትችሉ አትዘንጉ። ይህን ዓይነቱን ወሰን-አልባና ማለቂያ የለሽ ክህሎትና ብቃት አለው። ...መሆን ትችላላችሁ። የምትፈልጎቸው ነገሮች ሁሉ ሊኖራችሁ ይችላል። ጥበቃችሁንና ፍላጎታቸሁን አጎልብቱ።

17 days ago

ETB A

ድምጽ አሰምቶ ማልቀስም ራስን ለከፋ አደጋ ማጋለጥ መሆኑን ቀድመው ከታሰሩት ጓደኞቼ በመረዳቴ ድምጽ አልባ ዕንባዬን ከአጋሮቼ ጋር ሆኜ ተወጣሁት በተመሳሳይ አደጋ የሞቱት በአንድ ምሽት ብቻ ሃያ አንድ መሆናቸውን እንደዚሁ በምስጢር ስንረዳ ሟቾች በግፍ ተገድለው እንደ ውሻ ሬሳ አንዱ በአንዱ ላይ ተመሳቅለው ከምርመራው ክፍል ውጪ ከደጅ እንዳደሩና ዝናብ ሲመታቸው ካደረም በኃላ በውል ሳይነጋ በአንድ ግልጽ የፖሊስ መኪና ሬሳቸው ተጭኖ ባሕር ዳር ከተማ በተለያየ ቦታ ተንጋለው አልፎ አልፎ በአንዳንዶቹ ላይ "ነጭ ሽብርተኞች በቀይ ሽብር እንደመስሳቸዋለን!" የሚል ወረቀት ተጽፎባቸው ቀኑን ሙሉ ውለው በእስረኛ በተቆፈረ ጉድጓድ በጅምላ "ቤዛዊት" ከተባለ ቤተ መንግስት ጀርባ እንደተቀበሩም ሰማን። በየቦታው የሚሞቱትን ጓዶቻችን ሁሉ ከለበሱት ልብስና ጫማ ጋር ይቀበሩ እንደነበር ከአንድ ራሱን ከለወጠ ፖሊስ እኔ ብቻ ሰምቻለሁ። በዚህ ዓይነትና በተለያዩ አሰቃቂ አገዳደል ብዙዎቹ ሕይወታቸውን እንዲያጡ ሲደረግ ቀሪዎቹ በረቀቀ ዘዴ ቃል ስንሰጥና ስንደበደበ ጥርሳችንን ነክሰን ሳንወሸክት አጋጣሚውን አልፈነዋል። የሦስት ዓመት አስራቴንም እንደጨረስኩ ወደ ደጀን መጥቼ አሁን ድረስ በዚህ ስራ እኖራለሁ።


Page 4 of 17
(Showing 31 - 40 of 162 products )