ETB A
ኢትዮጵያ የሱዳንን ውንጀላ አጣጣለች‼
📌 በሱዳን ጦር ላይም ተመሳሳይ ክስ አቀረበች‼
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሱዳን መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ የቀረበውን ክስ መሰረተ ቢስ ሲል ውድቅ አደረገው።
ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ፣ ሱዳን የእርስ በርስ ጦርነቱን ተጠቅማ ለህወሃት ቅጥረኛ ወታደሮች መጠጊያና ድጋፍ በመስጠት በኢትዮጵያ ላይ ትንኮሳ እንዲፈጽሙ እያደረገች መሆኑን አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ከታሪካዊ የህዝቦች ወዳጅነት በመነሳት እስካሁን ታግሳ እንደቆየች የገለጸው መግለጫው፣ ሱዳን ለፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች መናኸሪያ ሆና ማገልገሏን አውግዟል።
ይህ ድርጊት የውጭ ኃይሎችን እኩይ አጀንዳ ለማሳካት ያለመ መሆኑን የጠቆመው መግለጫው፣ ኢትዮጵያ የሱዳን ግጭት በውይይት፣ በሰብዓዊ ዕርዳታና በሲቪል አስተዳደር እንዲፈታ ያላትን ጽኑ አቋም አረጋግጧል።
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
👇👇👇
https://t.me/gate22522